የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

logo

አዲስ አበባን በመለወጥ ላይ

picture of Construction picture of Construction


አዲስ አበባን በማዘመን ላይ

picture of Construction picture of Construction

ማስታወቂያ

የ11ኛውን ዙር ዕጣ ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው በቦሌ አራብሳ፣ በኩዩ ፈጬና በቂሊንጦ የተገነቡ የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝግበው ለሚጠብቁ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ዕጣ የሚወጣባቸው መሆኑ ነው፡፡

ለአካል ጉዳተኞች ለመጀመሪያ ጊዜ 5% ተደራሽ ቤቶችን በማዘጋጀት ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራርም በመከተል ላይ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም የቤት ልማት ፕሮግራሙ 30 በመቶ ለሴቶች ቅድሚያ በመስጠት የሴቶችን ተጠቃሚነት ከፍ ያደረገ ሥራ የሚሰራ ሲሆን 20 በመቶ ለመንግስት ሠራተኞች ቅድሚያ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለመጀመሪያ ጊዜ በልደታ ሳይት ባለ 12 ወለል (G+12) የጋራ መኖሪያ ህንፃ ደረጃውን በጠበቀና በጥራት ሠርቶ ያጠናቀቀ ሲሆን ህንፃው 127 ቤቶችን ይዟል፡፡

የዕጣ ማውጣት ስነስርኣቱ እንድተጠናቀቀ የእድለኞችን ዝርዝር የምናስታውቅ ይሆናል፡፡